ሶርያ ከእስራኤል የሚሳይል ጥቃት እንደተሰነዘረባት አሰታውቃለች። የሀገሪቱ ጦር ኃይል እንዳስታውቀው ሚሳይሎች በሰሜናዊው የአሌፖ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ እና በደማስቆ አቅራቢያ የሚገኙ ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
ይሁን እንጂ ከቁሳዊ ጉዳት ባለፈ ሰዎች ላይ ጉዳት አለማድረሱ ተገልጿል። ሚሳኤሎች ከሚድትራኒያን ባህር አቅራቢያ እና ከሰሜን እስራኤል ከገሊላ ባህር የተወነጨፉ ናቸው ተብሏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-09-01
