ሀገሬ ቲቪ

የዛፖሬዚያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እየተመረመረ ነው

ሩሲያ እና ዩክሬን ከኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያው አቅራቢያ ለተፈጸሙ ተኩሶች አንዱ ሌላውን ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል።

ሩሲያ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ የጀመረችውን እንቅስቃሴ "ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን " ብላ ትጠራዋለች ኦፕሬሽኑ የዩክሬን ጽንፈኞች ማስወገድንና ሩስያውያን መጠበቅን ያለመ ነው ።

የዩክሬን የኒውክሌር ኩባንያ ኢነርጋቶም እንዳስታወቀው ዛፖሪዝሂያ ሬዲዮ አክቲቭ መሳሪያዎች ያሉበትን ቦታ ጨምሮ አምስት ቦታዎች ላይ ጥቃት ደርሶበታል ብሏል፡፡

ሩሲያ ግን ዛፓሬዚያ ላይ ለደረስው ጥቃት ዩክሬን ትከሳለች እኔ አይደለሁም በሚል። ፋብሪካውን ማጥቃቷን እና ስራ ማስተጓጎሏን ገልጻለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን ከሁለቱ መካሰስ በላይ የኒኩለር ኅይል ማመንጫው ደህንነት እረፍት ነስቶታል ዳፋው ለበዙዎች ይተርፋልና ።ልዚህም ነው ባለሞያዎች በኒውክሌር ኃይል ማመንጫው ተገኝተው ጣቢያው መመርመር የሚችሉበት እድል በአስቸኳይ እንዲፈጠር ሲወተውት የነበረው።

በዚህም ሁለቱም አካላት በአካባቢ ውጊያ እንዲያቆሙ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።ይህ ውትወታው ተቀባየነት አግኝቶ የተባበሩት መንግስታት ቡድን የዩክሬን የኑክሌር ጣቢያ መጎብኘቱ ተነግሯል።

ወደ ስፍራው ያቀናው ቡድን በዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማሪያኖ ግሮሲ የተመራ ነው።

የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማሪያኖ ግሮሲ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ በሰጡበት ይህንን ተናግረዋል።

“ቡድኑ በፋብሪካው ስላለው ሁኔታ ገለልተኛ ና ትክክለኛ ግምገማ በቅርቡ ይፋ ያደርጋል ። የቡድኑ በፋብሪካው መቆየት ምክንያቱ ይሄ ነው ሲሉ” ተደምጠዋል።

የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማሪያኖ ። ጉብኝቱ ቦታውን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆንም ያለመ ነው ተብሏል።

ጣቢያው በዩክሬን የሚገኝ ይሁን እንጂ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ነው ።ነገር ግን ዩክሬናውያኑ የጣቢያው ሰራተኞች በተቋሙ የሚሰሩትን ሥራ እንደወትሮ እየሰሩ መሆኑ ይነገራል። ሩሲያ ቦታውን የተቆጣጠረችው ከስድስት ወር በላይ በፈጀው ጦርነት መጀመሪያ ላይ ነው።

ምዕራባውያን ለዩክሬን እንዲሰጥ እየወተወቱ ቢሆንም ለሩሲያ የሚዋጥላት ኣልሆነም። የኒውክለር ተቆጣጣሪ ቡድኑ በዛፖረዚያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ለመድረስ በርካታ ሰአታት ጠብቋል ነው የተባለው ።

የመዘግየቱ ምክንያት በአቅራቢያው የሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች በፈጠሩት ግርግር ነው ተብሏል። ቡድን በቦታው ላይ ያለውን የጉዳት ደረጃ እና የዩክሬን ሰራተኞችን ሁኔታ ለመገመገም እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አልጀዚራ ጽፏል።

ሩሲያ ተቋሙን ኃይሏን ለማጠናከር ከሩሲያ የሃይል አውታር ጋር ለማገናኘት አቅዳለች በሚል በዩክሬን ትወቀሳለች። ሞስኮ በበኩሏ ይህንን ይህን አትቀበልም ።

ይሁን እንጂ ወታደሮቿን ከጣቢያው እንድታስወጣ የሚቀረቡ ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን እንዳልሰማ እያለፈች ነው ። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሞስኮ ፋብሪካው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲሠራ እና የኤጀንሲው ተቆጣጣሪዎች ተግባራቸውን እንዲያጠናቅቁ ለማድረግ ሁሉንም ነገር እያደረገች ነው ብለዋል ።

በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን የሚገኘው ዛፖሬዚያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ በአውሮፓ ትልቁና በዓለም ላይ ካሉት 10 ትላልቅ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያዎች መካከል አንዱ ነው።

በመቅደስ እንዳለ
2022-09-02