ሀገሬ ቲቪ

በታራሚዎች ላይ የሚፈጸም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት

በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ታራሚዎች ላይ የተወሰኑ የፖሊስ አባላት በታራሚዎች ላይ የሚፈጽሙት የስድብ፣ ማስፈራራት፣ ዛቻ እና የድብደባ ድርጊቶች መኖራቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ላይ ባከናወነው ክትትል እና ይፋ ባደረገው ሪፖርት ነው ይኽ የተመላከተው።

በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉ ወጣት አጥፊዎች፣ ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች በየፈርጅ ተለይተው አለመያዛቸው ሌላው ችግር እንደኾነ ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

በተጨማሪም ለአካል ጉዳተኛ ታራሚዎች፣ ሕፃናት እና ታማሚዎች በልዩ ሁኔታ የሚደረግላቸው ድጋፍም ሆነ እንክብካቤ አነስተኛ ነው ብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-02