በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ከቀረጥ ነጻ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች መሸጫ ሱቅ ተከፈተ።
ሱቆቹ በአየር መንገዱ የሚጓዙ ደንበኞች የሚፈልጉትን የቆዳ ውጤቶች ከዚያው መሸመት የሚያስችላቸው ነው።
ምንም እንኳን ፕሮጀክቱ ጅምር ቢሆንም ባለፉት ሁለት ወራት 200 ሺ የአሜሪካን ዶላር ከሽያጭ ማዕከሉ መገኘቱን የኢንዱስተሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።
ከቀረጥ ነጻ የቆዳ ውጤቶች የሽያጭ ማዕከል በ195 ካሬ ስኩየር ሜትር ላይ ያረፈ ነው። በ2014 በጀት ከቆዳና ቆዳ ውጤቶች ወጪ ንግድ 40.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-09-02
