የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ተባለ። የአባይ ተፋሰስ የላይኛው አባል ሀገራት የመጀመሪያው ከፍተኛ የትብብር ኮንፈረንስ ዛሬ ተጀምሯል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓባይ ተፋሰስ አባል ሀገራት በወንዙ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ትብብራቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።
ይህም እውን እንዲኾን ምሁራን ፣ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና ጋዜጠኞች የበኩላቸውን አስተዋጻኦ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-09-05
