የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር ተመሰረተ። በአምራች አርሶ አደሩ በኩል የሚነሱ የግብአት አቅርቦት ችግርን መፍታት፣ በዓለም ገበያ መቀዛቀዝ ምክንያት አርሶ አደሩ እንዳይጎዳ የመድን ተጠቃሚ ማድረግ የማህበሩ ቀጣይ ትኩረቶች ናቸው ተብለዋል።
ማህበሩ ለቡና ልማቱ ብሎም አርሶ አደሩን ለመደገፍ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ገልጸዋል። ብሄራዊ ማህበሩን ለመመስረት የአራት አመት ዝግጅት ስለመደረጉም ተነግሯል።
በአብርሃም በለጠ
2022-09-05
