
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሁለት ሳምንታት በፊት በተካሄደው ምርጫ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የዊሊያም ሩቶን ፕሬዝዳንትነት አጸደቀ።
የኬኒያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪ የነበሩት ራያላ ኦዲንጋ መሸነፋቸውን ተከትሎ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ለሀገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ክሳቸውን አቅርበው ነበር።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ በሰጠው ውሳኔ ምርጫው ስለመጭበርበሩ የሚያሳይ ማስረጃ አላገኘሁም ሲል የራያላ ኦዲንጋን ክስ ውድቅ አድርጎታል።
ኬኒያን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለ አስር ዓመት ሲያስተዳድሩ የነበሩት ዊሊያም ሩቶ በዘንድሮ ምርጫ ማሸነፋቸውን ደግሞ በይፋ አጽድቋል ሲል ደይሊ ኔሽን ዘግቧል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-05