ሀገሬ ቲቪ

ብሪታንያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አገኘች

ሊዝ ትሩስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ። ትሩስ ተፎካካሪያቸው ሪሺ ሱናክን 81 ሺህ ለ60 ሺህ በሆነ ድምጽ በመብለጥ ነው ያሸነፉት።

አሽናፊዋ ጠቅላይ ሚንስትር በሀገሪቱ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እስራለሁ ብለዋል ። የግብር ቅነሳም ከሰራቸው ቅድሚያ የሚሰጡት እንደሆነም ተናግረዋል።

አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የመተማመኛ ድምጽ በማጣት ከስልጣን በመወገዳቸው ለሳምንታንት የተፈጠረውን ከፈተት የሚሞሉ ይሆናል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-05