ሀገሬ ቲቪ

ዳዎን ሲንድሮም ያለባቸውን የፊት ገጽታ የተላበሱ አሻንጉሊቶች

የሰው ልጆች በተፈጥሮ 23 ጥንድ ወይም 46 ዘረመሎች አሏቸው። ከነዚህ 23 ጥንድ ዘረመሎች ውስጥ ሁለቱ ጥንድ ዘረመሎች ለሰው ልጅ ዘር ለመተካት የሚረዱ መረጃዎችን ሲይዙ ቀሪዎቹ 21 ጥንድ ዘረ መሎች ደግሞ ከመራቢያ ውጭ ያሉትን የሰውነት ክፍሎች በትክክል ከተፈጠሩ በሗላ ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ የሚያደርጉ መረጃዎችን የሚይዙ እንደሆኑ ሳይንስ ይናገራል።

ታዲያ በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሰራሽ እነዚህ ዘረመሎች ላይ አደጋ ሲፈጠር በውስጥ የማይታዪ እና በውጭ የሚታዩ የሰውነት ቅርጽ ላይ ችግር ይፈጠራል ። በእንደዚህ አይነት የዘረመል ችግር ከሚከሰቱት በሽታዎች መካከል ደግሞ ዳዎን ሲንድሮም አንዱ ነው።

ዳዎን ሲንድሮም የአካል እና የአዕምሮ እድገት ውስንነትን እና የተለያዩ የጤና እክሎችን የሚያስከትል ህመም ሲሆን ከ800 ሕፃናት ውስጥ አንዱ ከዚህ ችግር ጋር እንደሚወለድ ጥናቶች ያመለክታሉ ።

የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰወችም ትንሽ የራስ ጭንቅላት ፤ ሎጫ ና ስስ ፀጉር ፤ ትንሽ እና ከተለመደው ቦታ የወረደ ጆሮ ፤ ድፍጥጥ ያለ አፍንጫ እና ተለቅ ያለ ምላስ በፊት ገጽታቸው ላይ ይላበሳሉ ።

ታዲያ የዚህን ህመም አስከፊነት የተረዳች አንዲት ዲዛይነር የነሱን የፊት ገጽታ የተላበሱ አሻንጉሊቶችን በመስራት ለገበያ ማቅረቧ ተሰምቷል ።

ሴፍ ሃማዴህ የተባለች ሶሪያዊት በተለያዩ የልጆች መጫወቻ ሱቅ ስገባ ተመሳሳይ እና የተስተካከለ የፊት ገጽታ የተላበሱ አሸንጉሊቶችን ብቻ ማየቴ ይህን እንድሰራ አስገድዶኛል ያለች ሲሆን አሁን ላይ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆኑ ህጻናት እንዚህን አሻንጉሊቶች ሲያዩ ደስተኛ እንደሚሆኑ ትናገራለች ።

ዳውን ሲንድሮም ያለባቸውን ልጆች በቀላል ነገር ማስደሰት ይቻላል እስከዛሬ ይህ አለመደረጉ አሳዛኝ ነው ። አሁን ወደ ሱቅ ገብተው እነሱን የሚመስል አሻንጉሊት ሲያገኙ በጣም ደስ ይላቸዋል ።

አሁን ላይ እንዚህ አሻንጉሊቶች ከ 22-30 የአሜሪካ ዶላር እየተሸጡ ሲሆን ከሽያጩ የሚገኘው ትርፍም በዚህ ህመም ተጠቂ የሆኑ ልጆችን ለሚረዱ ግብረሰናይ ድርጅቶች ገቢ እየተደረገ ነው ተብሏል ። ልጇ የዚህ ህመም ተጠቂ የሆነች አንዲት ሴት እነዚህን አሸንጉሊቶች በመመልከቷ የተሰማትን እንዲህ ትገልጻለች ።

ይህ መደረጉ ሌሎች ዳውን ሲንድሮም ያለባቸውን ሰዎች ይበልጥ እንዲያውቁና ስለነሱ እንዲጨነቁ ያበረታታል። ልጆቹም በጣም ደስ ብሏቸዋል ። በጣም ግሩም ሐሳብ ነው ። ደግሞ እንዲ ውብ ይሆናሉ ብዬ አልጠበኩም ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-05