ሀገሬ ቲቪ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አቀባበል

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሐምሌ 9 2014 ዓ.ም ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ለሕክምና ወደ አሜሪካ መሔዳቸው ይታወሳል።

ቅድሱነታቸው ሕክምናቸውን ተከታትለው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ለክበራቸው በተዘጋጀው የአቀባበል ስነስራት ላይ ንግግር ያደረጉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ሕመሙ ይበልጥ እንዲሻለኝ መቆየት ቢገባኝም እመለሳለሁ ባልኩት ቀን መጥቻለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን የተከበረች ናት ያሉት አቡነ ማትያስ የቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት መከበር እንዳለበትም ተናግረዋል። በሕክምና ጉዞዬ ላይ በርካታ ሰዎች እንዲጠራጠሩ ኾነዋል። እንዲህ መኾኑ አግባብ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል ።

ለሕክምና ጉዞ በሔዱበት ወቅት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅርስን ያለ ፈቃድ ሊያወቱ ነው በሚል የተፈጠረው ግርግር እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-06