የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የወደሙ የሕክምና ተቋማትን ማቋቋሙን ለእኔ ተውት አለ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አስታደደር አባላት እና ተወካዮች የህክምና ግብዓቶችን እና ሰብዓዊ ድጋፍ ይዘው ወደ ሰሜን ሸዋ አቅንተዋል በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሓት በዞኑ ያወደማቸውን 10 የህክምና ተቋማት ሥራ ለማስጀመር በመጀመሪያ ዙር 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍና የህክምና ግብዓቶች አድርገዋል የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የወደሙት የጤና ተቋማቱ ሙሉ ለሙሉ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ግብዓት ለማሟላት ኃላፊነት ወስጃለሁ ብሏል የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባደረገው ጥሪ መሰረት በዞኑ የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማቋቋም ክልሉ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተጠቁሟል የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-29
