እንደተረቱ ነው፤ መጀመሪያ መቀመጫዬን እንዳለችው። ሰዎች ጎናቸውን የሚያሳርፉበት፤ የሚጠለሉበት ማረፊያ ወይም ቤት ይፈልጋሉ።
ይህ ሰው ኒሲም ይባላል። በእስራኤል የሚኖረው ኒሲም ሰዎች ጎናቸውን የሚያሳርፉበት ቤት ለመስራትም ሆነ ለመከራየት አቅም የሌለው ምስኪን።
ታዲያ በሄርዝሊያ የባሕር ዳርቻ ላይ የራሱን የሆነ ማረፊያ ዋሻ አበጅቶ መኖር ከጀመረ ዘመናትን ተሻግሯል። በኖሪያውን በባህር ዳርቻው ላይ የገነባው ጎልማሳ አሁን በሀገሬው ባለስልጣናት የተወደደም አይመስል፤ ዘመናትን ከኖረበት ቤቱ እንዲወጣ መስጠንቀቂያ ሰጥተውታል። ያለፈቃድ ህገወጥ ግንባታን ገንብተሃል በሚል። ኒሲም ግን በዚህ አይስማማም።
“ላደረኩት ነገር ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ይልቅ ወደ ፍርድ ቤት ነው የወሰዱኝ። እኔ እዚህ ሙዚየም ነው የገነባሁት።”
በሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ሚንስቴር ዋሻውን ለቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያም ተሰጥቶታል። እንደ ሚንስቴሩ ከሆነ ኝባታው በጣም አደገኛ እና አካባቢን አደጋላይ የሚጥል ነው።
ወደ 50 ዓመታት ለሚጠጋ ግዜ በዋሻው የኖረው ሰው ከዋሻው ግድግዳ ላይ አንዳች ነገር ወድቆበት እንደማያውቅ ይናገራል። በዋሻው ላይ የሚታይ አንዳች እንኳን ስንጥቃት የለም በማለትም የቱጋር ነው የኔ ዋሻ ጉዳቱ ሲል ይሞግታል።
“ምስጋና ለአምላክ ይግባና ሁሉም ነገር ጠንካራ ነው”
በቦታው በርካታ የምህንድስና ባለሙያዎች ይገረማሉ። የሚለው ነሲም የከተማው የምህንድስና ባለሙያዎች መጥተው ተመልክተውት እንደነበርም ያወሳል።
እንዴት ባልኮኒዎቹ በአየር ላይ ሊቆሙ ቻሉ ሲሉም ይጠይቁኛል ሲልም ይናገራል። እራሴን በራሴ ነው ያስተማርኩት የሚለው ነሲም ከገዛ ስህተቶቹ እየተማረ ዋሻውን እዚህ እንዳደረሰው የቢቢሲ ዘገባ አትቷል።
ይህንን ዋሻ ለመገንባት ተፈጥሯዊ ግብዓቶችን እና ዳግም አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ ቁሶች ጥቅም ላይ ውለዋል። ከውጪ ሲመለከቱት አንድ ቄንጠኛ መዝናኛ የሚመስለው የነሲሙ መኖሪያ፤ ውጫዊ ገፅታው በተሰባበሩ ሴራሚኮች እና ብርጭቆዎች የተጌጠ ነው።
ይህ ሰው የገነባው መኖሪያ በበርካታ ቱሪስቶችም ጭምር የመጎብኘት እድል የገጠመው ነበር። ቦታው ለመጎዳቱ ተጠያቂው እኔ አይደለውም የሚለው ነሲም የሀገሬው ባለስልጣናት ለተፈጥሯዊ ምህዳሩ መበላሸት ተጠያቂ ናቸው ባይ ነው።
ባለ ስልጣናቱ ግን የነሰም ቤት ከፍታ ለመደርመስ የተጋለጠ ነው እና በአፋጣኝ መልቀቅ አለበት። ነሲም ግን ከ40 ወይም ከ50 ዓመታት በፊት ነግረውኝ ቢሆን እኔም አልሞክረውም ነበር፤ አሁን ኝ ምን ሲደረግ እያለም ይገኛል።
የነሲም ደጋፊዎች ታዲያ አሁን እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፤ ቤቱ እንዳይፈርስ እና እንደ ሀገር ቅርስ እንዲመዘገብ ለማድረግ።
በሳምሶን ገድሉ
2022-09-07
