ሀገሬ ቲቪ

ሩሲያና ቻይና ለነዳጅ መገበያያ ዶላርን ላለመጠቀም ወሰኑ

ሩሲያና ቻይና ለነዳጅ መገበያያ ዶላርን ላለመጠቀም ወሰኑ።

የሩሲያ ግዝፉ የነዳጅ ኩባንያ ጋዝፕሮም ቻይና የጋዝ ግብይትን በሩሲያ ሩብል ወይም በቻይና ዩዋን እንድተክፍለው የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል ሲል ሲኤን ኤን ዘግቧል።

ሁለቱ ሀገራት ከዶላር ውጪ ለመገበያየት የወሰኑት ሩሲያ ዶላር እና ዮሮን ጨምሮ ከምዕራባዊያን መገበያያዎች ራስዋን ለማላቀቅ ነው ተብሏል።

ፑቲን የአውሮፓ ደንበኞቻቸው ከሩሲያ ጋዝን መግዛት ከፈለጉ በጋዝፕሮም ባንክ የሩብል የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-07