በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ ሰጪነት ከዩክሬን የተገዛውን የእርዳታ እህል የጫኑ 60 የጭነት መኪኖች ኢትዮጵያ ደረሱ።
ባለፈው ሳምንት ጅቡቲ ወደብ የደረሰችው መርከብ የጫነችውን እህል ካራገፈች በኋላ በጭነት እህሉ ዛሬ ኢትዮጵያ ደርሷል።
ይህም የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ወደ አፍሪካ የደረሰ የመጀመሪያው የእህል ጭነት ነው።
ኢትዮጵያ የደረሰው የስንዴ አቅርቦት ከአንድ ሚሊዮን ተኩል በላይ በችግር ላይ ያሉ ሰዎችን ለአንድ ወር ያህል ለመመገብ የሚረዳ መሆኑን የአለም ምግብ ፕሮግራም ተናግሯል።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ ያደረሱት "ቁጣ" ትክክል አይደለም ብለዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-09-07
