ዓለምን በእሀል እና በነዳጅ እጥረት ዋጋ እያስከፍለ ያለው የሩሲያን የዩክሬን ጦርነት 201ኛ ቀኑን ደፍኗል። በዚህ ሁሉ ቀናት የሩሲያ የበላይነት አይሎበት የነበረው ጦርነት አሁን የዩክሬን ጦር በመልሶ ማጥቃት የበረታበት መስሏል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፤ወታደሮቻቸው በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የተወሰኑ ገዛቶችን ነጻ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ እርምጃው የሩሲያ ኃይሎች ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ለመልቀቅ እንዲገደዱ እንዳደረጋቸወም እየተገልጸ ነው፡፡
የሩሲያ ጦር በካርኪቭ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሃይሎችሁን በደንብ ለማደራጀትና ለማስታጠቅ ሲል ለማፈገፈግ መገደዱን ገልጿል። ይህ ለጊዜውም ቢሆን ሁሉንም የሉሃንስክ እና የዶኔስክ ክልሎች ለመያዝ የሚደርገወን ጥረት እነደሚያዘገየው ነው የሩሲያ ጦር የገልጸው።
ዩክሬናውያኑ ግን አቅማችንን አጠናክረን የወሰድነው እረምጃ ያመጣው ለውጥ ነው እያሉ ነው ።ሆኖም ቀረ አንድ ነገር እርግጥ ሆኗል የሩሲያ ጦር በመጋቢት ወር ከተቆጣጠሩት የዩከሬን መሬቶች ማፈግፈግ መጀመራቸው። ይህን ተከትሎም በአንዳንድ የዩክሬን መንደሮች የዩክሬንን ባንዲራ ከፍ ብለው ሲያወለበልቡ ታይተዋል ።
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ፤ እየተገኙ ያሉ ድሎች የዩክሬን ኃሎች የሩሲያ ጦርን ማሸነፍ እንደሚችሉ አማላካች ናቸው ብለዋል፡፡ ጦርነቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ምዕራባውያንና የዩክሬን አጋሮች የሚያደርጉት የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ተማጽነዋል፡፡
ለሎች ምረጃዎች ደግሞ የሩሲያ ጦር አቅሙን ለማደራጀት ቦታዎችሁን መልቀቁን ሸመላክች ነው ምክኛቱም 48 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ከተወስዱበት መሬቶች ግማሹን ማስለቀቁን እየዘገቡ ነው።
ይህ በእንዲ እንዳለ ዩክሬን ምሰራቃዊ ክፍልም የሃይል አቅርቦት ተቋርጧል። ከርኪያቭ እና ዶንሲክ ሙሉ በሙሉ ሃይለ የተቋረጠባቸው ከተሞች ናቸው። በዚህም ከ9 ሚሊይን በላይ ሰዎች ከሃይል አቅርቦት ውጪ ሆነዋል።
የዩክሬን ሩሲያ ሆን ብላ የሃይል ማመንጫዎችን እና የህዝብ መሰረት ልማቶቸን በሚሳኢል መታብኛለች ስትልት ከሳለች የኃይል ምቋረጡ መንሳኤም እርሱ እንደሆነ በመግልጽ ።
ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ካርኪቭ ቲኢሲ-5ንየ ሃይል ማመንጫ ሩሲያ መትታለች ሲሉ ጣቢያው በእሳት ሲያያዝ የ ሚያሳይ ምስልን አጋርተዋል ይህም የሃይል ጣቢያ የሀገሪቱ ሁለተኛው ትልቁ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ነው ።
ብርዱ በሚያይልበት ምስራቅ አውሮፓ ኤሌትሪክ ከብርሃን ስጭነት ባለፈ ብርዱን መቋቋሚያ ሙቀት የሚለግስ በመሆኑ የኤለትሪክ መቋረጡ የዜጎችን ህይወት ያከበደዋል የሚል ስጋት ደቅኗል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-12
