በአይን ህክምና ላይ ያለውን ረዥም ቀጠሮ የሚያስቀር የህክምና ማእከል ተመረቀ። በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል በ461 ሚሊዮን ብር ወጪ በሀገሪቱ ትልቁና ዘመናዊ የአይን ህክምና ማእከል ለአገልግሎት ብቁ ሆነ።
የሕክምና ማዕከሉ በ8 የተመላላሽ ክፍሎች ውስጥ ህክምና ሲሰጥ የነበረውን ወደ 33 ክፍሎች ከፍ የሚያደርግ እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኀበራዊ ገጻቸው አስታውቀዋል።
ከዚህ ቀደም የነበረውን 40 የመኝታ አልጋዎች አሁን ላይ ወደ 120 ከፍ እንዲልም ሆኗል ብለዋል። በአይን ህክምና ላይ ሲታይ የነበረውን ረዥም ቀጠሮ የሚያስቀርና እንግልት የሚቀንስ፣ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሪፈር የሚመጡትን በተደራጀ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ማዕከሉን የተለየ ያደርገዋል ተብሏል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-09-12
