ሀገሬ ቲቪ

ከ49 ሺሕ እስከ 4መቶ ሺሕ ብር የሚያወጣው እራት

የታላቁ የሀገር ቤት ጉዞ አካል የሆነ የእራት ግብዣ በታላቁ ቤተ-መንግስት ተዘጋጀ፡፡ እራቱ ከ49 ሺሕ እስከ 4መቶ 41 ሺሕ ብር ዋጋ ተተምኖለታል አራት የዳያስፖራ ማህበራት ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያዊ ኤምባሲ እና ዳያስፖራ ኤጄንሲ ጋር በመተባበር ነው ፕሮግራሙን ያዘጋጁት፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡ ከእራት ግብዣው የሚገኘው ገቢም በኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል ነው መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል በዚህ የእራት ፕሮግራም ላይ በቡድንም ሆነ በግል ለመሳተፍ አይዞን ኢትዮጵያ ዶት ኮም በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በመግባት ትኬቱን መግዛት ይችላሉ ጥር 8 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ለሚካሄደው የእራት ግብዣ ዋጋም በነጠላ መቀመጫ 49 ሺሕ ብር ፣ ቪአይፒ መቀመጫ 98 ሺሕ ብር አስር መቀመጫ ደግሞ 4 መቶ41 ሺሕ ብር ዋጋ ወጥቶላቸዋል ለስፖንሰሮችም የተዘጋጀ እድል መኖሩ የተገለጸ ሲሆን አንደኛ ደረጃ 20 ሺህ ዶላር፣ ሁለተኛ ደረጃ 15 ሺህ ዶላር እንዲሁም ሶስተኛ ደረጃ 10 ሺህ ዶላር መሆኑ ታውቋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-29