ሀገሬ ቲቪ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዳማ እና ባሕር ዳር ሙከራ ጀመረ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዳማ እና ባሕር ዳር ከተሞች የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ።

ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች ያደረጋቸዋል፡፡

የአዳማ እና ባሕር ዳር ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርድ ደንበኞች ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል የያዘ መሆኑም ተገልጿል።

ይህ የባሕር ዳር እና አዳማ ከተሞች የደንበኞች ሙከራ እስከ ሚያዝያ 2015 ድረስ በ25 ከተሞች አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚያደረገው ሒደት አካል መሆኑንም ገልጿል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-12