ሀገሬ ቲቪ

ኡጋንዳ 65 ሚሊዮን ዶላር ለኮንጎ ከፈለች

ኡጋንዳ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የ65 ሚሊዮን ዶላር ከፈለች። ክፍያው በጦር ክፍያ ካሳነት የተከፈለ ሲሆን ኡጋንዳ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 325 ሚሊዮን ዶላር የጦር ካሳ እንድትከፍል የዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) ከወራት በፊት ወስኖባታል።

የከፈለችው 65 ሚሊዮን ዶላርም የመጀመሪያ ዙር የካሳ ክፍያው ነው። ኡጋንዳ ይህ ውሳኔ የተላለፈባት ከ20 ዓመታት በፊት የመከላከያ ኃይሏ በኮንጎ ባደረገው ወረራ እና ዝርፊያ ላደረሰው የህይወት መጥፋት እና የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ ነው ተብሏል። ክፍያውም እስከ 2026 እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ሲል የዘገበው ዘ ኢስት አፍሪካን ነው።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-12