ኒው ዮርክ የፖሊዮ ስርጭትን በመስጋት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች። የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (CDC) በቆሻሻ ውኃ ላይ ባደረገው ጥናት በኒውዮርክ በርካታ ቦታዎች የቫይረሱ ናሙናዎችን ማግኘቱን ይፋ አድርጓል ።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይም አንድ ሰው በፖሊዮ ቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ። ለዚህ ነው ኒውዮርክ በፖሊዮ ሳቢያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማውጅ የተገደደችው ።
ፖሊዮ በአሜሪካ ሲታይ ከአስርት ዓመታት በኋላ ነው ተብሏል። አሜሪካ የዛሬ 50 ዓመት በፊት ነበር ከፖሊዮ ነጻ ሀገርነቷን ያውጀችው።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-12
