ሀገሬ ቲቪ

ከ50 ሚሊየን በላይ ሰዎች በዘመናዊ ባርነት ውስጥ ይገኛሉ

ዘመናትን የተሻገረው ባርነት በአፍሪካና ሌሎች ደሃ ሃገራት ጉልበቱን አጽንቶ ከቆየበት በህዝቦች ያልትቋረጠ ትግል በ19ኛው ከፈለ ዘመን የቋጨ ቢመስለም ዘምናዊ ባረነት ዛሬም ሽይሏል ይላል የትባበሩት መንግስታት አዲስ ያው_አው ሪፖርት።

ተመድ እንደሚለው ከ50ሚሊዮን በላይ ዜጎች በዘመናዊ በባርነት ውስጥ ናቸው ። ይህም ማለት ሳይወዱ በግድ በሚሰሩት ስራ ጉልበታቸው ይበዘበዛል አልያም ለግዳጅ ትዳር ተገደዋል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በአለማች በአሁኑ ግዜ ከ150 ሰወች ወስጥ አንዱ በግዳጅ ሰራ ይሰራል ወይንም ተግደው በገቡበት ትዳር ወስጥ ይገኛሉ ።

ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርትም ከ27.6 ሚልየን በላይ ሰዎች በግዳጅ ሰራ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ወስጥም 3.3 ሚሊየን የሚልቁት ህጻናት ናቸው በሎል። ግማሽ ያሀሉም በወሲብ ንግድ ወስጥ እንዲሰማሩ የተገደዱ ናቸው ።

የተቀሩ 22 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎችደግሞ ተገደው በገቡበት ጋብቻ ወስጥ አለፍላጎታቸው ይኖራሉ ከእነዚህም ወስጥ ሁለት ሶስተኛው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው እድሚያቸውም በአማካይ ከ 15 እንደማይበልጥ ሪፖርቱ ያሰርዳል ።

በተመድ በሪፖርቱ 65 በመቶ የሚሆንው አስገዳጅ ጋብቻ በእሲያ እና በ ፓስፊክ የሚገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ በአፈሪካ ፣በአረብ እና በአውሮፓ ናቸው በሏል። 85 በመቶ የሚሆኑት በግሉ ዘርፍ ውስጥ በአሰገዳጅነት ይሰራሉ ከእነዚህ ወስጥም 23 በምቶው በወሲብ ንግድ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ።

ከ2016 እስክ 2021 ባለው አመት ብቻ 10ሚሊየን ዜጎች ወደ ዘመናዊ ባርነት ተቀላቀልዋል ይላል ሪፖርቱ ይህ ቁጥርም ከ 5 አመት በሃላ የ6.6 ሚልየን ጭማሪ አሳይቷል።

የዓለም አቀፉ የሰራትኞች ድርጅት (ILO) ኃላፊ ጋይ ራይደር "የዘመናዊ ባርነት ሁኔታ አለመሻሻሉ አስደንጋጭ ነው" ሲሉ ሃሳብቸውን ሰጥትዋል።

በጣም ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ 50 ሚሊዮን ዜጎች በነዚህ ሁለት የባርነት ክሎች ውስጥ ይገኛሉ። ይህም በ2017 ከነበረው መጠን ይልቃል ከ2.7 ሚልየን ዜጎች በአሰገዳጅ ሰራ ውስጥ እንዲሁም ከ6.6 ሚሊየን በላይ ሰወች ደግሞ በገዳጅ ጋበቻ ውስጥ ይገኛሉ እንደማለት ነው። ስለዚም በተሳሳተ አቅጣጫ እየሄድን መኾኑናችን መጥፎ ዜና ነው።

ተመድ በኮቪድ ሳቢያ የተከሰተ የሃገራት ይኢኮኖሚ መቀዛቀዝ፣ በየቦታው እይተከሰት ያለ ጦርነት ፣የአየር ንብረት ለውጥ ሰፊ አሰተዋጾ ለዘማናዊ ባረነት መስፋፋት ከፈትኛ አስተዋጽኦ አደርገዋል ብሏል።

ሪፖርቱ የተባበሩት መንገስታት ደርጅት በ2030 ዘመናዊ ባርንትን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ያቀደው እቅድም እንደማይሳካ አመላካች ነው ተብሏል።

ዘመናዊ ባርነቱ በአደጉት ሃገራት የከፈ መሆኑ ጉዳዩ አሁንም ለአለም እራስ ምታት እንደሆነ የሚቅጥል መሆኑን ያሳያል ተብሎለታል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-13