በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከየጅቡቲ የባህር ዳርቻ ጥበቃ ሀይል እና ብሔራዊ ባህር ሃይል ቅዳሜ እለት ራስ-ብር ከተባለው አካባቢ ወደ የመን የምትጓዝ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ጀልባን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በጀልባው 196 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ነበሩ ተብሏል። ኤምባሲው ከጅቡቲ የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ 767 ፍልሰተኞችን ህይወት ማትረፍ ችያለሁ ብሏል።
እነዚሁ ዜጎቻችን ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው ገብተዋል ብሏል ኤምባሲው፡፡ ሶስት የውጭ ዜጎችና አንድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ወንጀል ተጠርጥረው ለፍርድ ቀርበዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከየመን ወደ ጅቡቲ እንዲሁም ከጅቡቲ ወደ የመን በሚያደርጉት ጉዞ በጅቡቲ የባህር ጠረፍ ክልል በሚደርስ የጀልባ መገልበጥ አደጋዎች በርካታ ዜጎቻችን ለሞት እየተዳረጉ ነው ብሏል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-09-13
