ሀገሬ ቲቪ

በ133 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው የግብርና መሳሪያዎች መገጣጠሚያ ተመረቀ

በቢሾፍቱ ከተማ በ133 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር የግብርና መሳሪያዎች መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ፋብሪካ ዛሬ ተመርቋል።

የተለያየ መጠን ያለቸው 16 ሺህ 803 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ተደረጓል ይህም የግብርና ስራቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያግዝ ተገልጻል፡፡

በምረቃት ሥነ ስርዓቱ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን መገኘታቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ማኀበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-13