አሜሪካ ወደ ሀገሬ አትምጡብኝ ስትል ጥላው የነበውን ዕገዳ አነሳች የተነሳው የጉዞ እገዳ ለስምንት የደቡብ አፍሪካ ሀገራት ነው ተብሏል የጉዞ እገዳው የተነሳላቸው ሀገራት ውስጥ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ፣ ሌሶቶ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሞዛምቢክ እና ማላዊ ናቸው አዲሱ የኦሚክሮን ቫይረስ በዓለም ላይ መሰራጨቱን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት የጉዞ እገዳ አድርገዋል በተመሳሳይ የፕሬዝዳንት ጆባይደን አስተዳደር ባለፉት 14 ቀናት የውጭ አገር ተጓዦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡየሚከለክል መመሪያ አውጥቶ ነበር አሁን ላይ ታዲያ ፕሬዝደንት ባይደን ያለውን ችግር በመረዳት ለውጦች ማድረግ አላስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ የመጀመሪያውን መመሪያ የሚሻር ሌላ አዋጅ መውጣቱን አስታውዋል ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ስለ ኦሚክሮን ቫይረስ ይበልጥ በመረዳት የማዕከላዊ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ምክረሐሳብ እንሰጠ ሲቢሲ ኒውስ አስነብቧል የሲዲሲን ምክረ ሐሳብ በመቀበል እና ለአሜሪካ ጥቅም ሲባል የጉዞ እገዳ መመሪያውን እንሻሩት ፕሬዝደንት ባይደን አስታውቀዋል
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-29
