
በኬንያ ምርጫ አሸናፊ የሆኑት ዊልያም ሩቶ የፕሬዝዳንትነት ቃለ መሃላቸውን ፈጸሙ። የ55 ዓመቱ ሩቶ 5ኛው የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ሆነው ቃለ መሃላቸውን ሲፈጽሙ በርካታ ኬንያውያን በስታዲየም ተግኝተው ደስታቸውን ገልጸዋል ።
በጠባብ ውጤት በምርጫው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በስነ ስርዓቱ ላይ አልታደሙም። 50 ነጥብ 5 ለ 48 ነጥብ 8 በመቶ በሆነ ውጤት የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ቢሆንም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ምርጫውን ፍትሃዊ ነው ብሎ ጥያቄያቸውን ውድቅ እንዳደረገው የሚታወስ ነው።
በበዓለ ሲመቱ ላይ ለመታደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ታድመዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-09-13