ሀገሬ ቲቪ

የዳይኖሰር ቅሪቶች በጨረታ እየተሸጡ ነው

ግዜ ግዜ እየተካ፤ ዘመንም ዘመንን እየቀየረ ወደፊት ብወነጎደ ቁጥር በርካታ አዳዲስ ነገሮችን እንሰማለን። ከበርካታ ሚሊዮን ዓመታት በፊት ነበሩ ሲባሉ ሰምተናል፤ አስፈሪዎቹ ዳይኖሰሮች።

ታዲያ እኚሁ ፍጥረታት ቅሪታቸው አለበት የተባሉ ቦታዎችን ጭምር በማሰስ እንጎበኛቸው ዘንድ በሙዚየሞቻቸው ውስጥ ያቆሟቸዋል።

ይህም ብቻም አይደለም እነዚህ ፍጥረታት ተራምደውበታል የተባለውን ስፍራም ሳይቀር ከልለው ይኸው ከሚሊየኖች ዓመታት አስቀድመው የረገጡት መሬት ሲሉም ጎብኝዎችን ይጠራሉ።

አሁን ግን እነዚህኑ ግዙፍ ፍጥረታት በባለጠጎች ቤት መኖር ሊጀምሩ መሆኑን ሰምተናል። እነዚሁ ዳይኖሰዎች በመተናቸው ለቅንጡ መኖሪያ ቤት የሳሎን ጌጥ መሆን የሚችሉ ናቸው ተብሎላቸዋል።

በሚቀጥለው ወር በፓሪስ ለሽያጭ ይቀርባል የተባለው ይሄው የዳይኖሰር ቅሪተ አካል 495 ሺሕ ዶላር ዋጋን የተተመነለት ነው።

ከዚህ ቀደም በዚሁ የፓሪስ ማጫረቻ ሌሎች የዳይኖሰር ዝርያ የሆኑ ቅሪቶች ለገበያ ቀርበዋል። ይህኛው ቅሪት ግን በፊልሞች ላይ እንደምናያቸው አይነት የሆነ ርዝመቱም 1 ሜትር ከ 30 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም እንደሆነ ሮይተርስ በድረ ገጹ አስነብቧል። ወደ ኋላ ያለው ዝርማኔ ሦስት ሜትር እንደሆነም በዘገባው ተካቷል።

ታዲያ ይሄው የዳይኖሰር ቅሪት ባለጠጎች በሳሎናቸው ላይ ሊያኖሩት የሚችሉት እንደሆነ ተመላክቷል። ከ20 ሚሊዮን ዓመት አስቀድሞ ይኖር የነበረ ዳይኖሰር እንደሆነ የተነገረለት ቅሪተ አካሉ ለመሸጥ ወረፋውን እየጠበቀ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም በዚሁ የፓሪስ ማጫረቻ ሦስት ሜትር ከግማሽ ቁመት ያለው እና 10 ሜትር የሚረዝም ዳይኖሰር በጨረታ ለባለ ጠጊኦች መተላለፉን ዘገባው ጨምሮ አትቷል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-09-14