ሀገሬ ቲቪ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንሰቴር አዲስ የሲሚንቶ ዋጋ ተመን ይፋ አደረገ

ሚኒስቴሩ ተመኑን ያወጣው ፋብሪካዎች የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ያወጡት ዋጋ የተጋነነ በመሆኑ ነው። የሲሚንቶ እጥረት በመኖሩ ለመንግስት ፕሮጀክቶች የሲሚንቶ አቅርቦት ቅድሚያ እንደሚሰጥም ሚንሰትሩ ገልጸዋል።

በተዋረድም ለግል አልሚዎችም የሲሚንቶ አቅርቦት እንደሚኖራቸውም ተገልጿል። በአዲሱ የዋጋ ተመንም ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ተወስኗል።

ሚንሰቴር መሰሪያ ቤቱ አሁን ይፋ ይደረኩት የሲሚንቶ የዋጋ ተመን ፋበሪካዎች ለአቅራቢዎች የሚያደርሱበት ዋጋ ነው ነገር ግን በሰርጭት ወቅት የመጋዘን ኪራይ እንዲሁም የትራንስፖርትን ዋጋን ታሳቢ በማድርግ አቅራቢዎች ለተጠቃሚ ያቀርባሉ ተበሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙት የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢንዱስትሪ ግበአቶች ልማት ደርጀት (ኢግልድ) ምርቶቹን በአዲስ አበባ እንደሚያከፋፍሉ ተገልጿል።

የክልል መንግስታትም በመረጧቸው አከፋፋይ ድርጀቶች አማካኝነት ምርቶቹን ለተጠቃሚ ያቀርባሉ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-14