ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአራት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ 49,203 ተማሪዎቹን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ሜትሮ ፖሊቲያን ዩኒቨርሲቲ ፤በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ገልጻል።

ትምህርት ቢሮው በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል። በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በመቀጠልም የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች የሚፈተኑ ይሆናል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁሟል፡፡ መረጃወን ያገኝ ነው ከ ምሀርት ቢሮው ገጽ ነው ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-14