ሀገሬ ቲቪ

አይ.ኤም.ኤፍ የ31.9 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለማዳጋስካር ሊሰጥ ነው

የገንዘብ ድጋፉ የደሴቲቱን ምጣኔ ሃብት በእጅጉ ያግዛል ተብሏል ። ድጋፉ የሚጸድቀውም IMF የአገሪቱን የኢኮኖሚ ፕሮግራም ግምገግማ ማጠናቀቁን ካረጋገጠ በኋላ ነው።

ድጋፉ ከዚህ ቀደም የነበሩትን ጨምሮ ተቋሙ ለማዳጋስካር ያደርገውም የገንዘብ ደጋፍ ወደ 159.7 ሚሊዮን ዶላር ያደርሰዋል። የሀገሪቱ የዕድገት ምጣኔ ግን በ2022 መጠነኛ ቅናሽ እንደሚኖረው ተተንብዩል።

በአለም አቀፍ ደርጃ የተከሰተው የምግብና የነዳጅ ዋጋ በሀገሪቱ ያለውን የዋጋ ግሽበት ወደ 9.8 በመቶ እንደሚያሳደገው ነው የተገለጸው።

በሳምሶን ገድሉ
2022-09-14