ሀገሬ ቲቪ

መብረቅ እንደመታው ያላወቀው ግለሰብ

በተለያዩ ጊዜያት ከተፈጥሮም ከሰው ሰራሽ አደጋዎች ጋር በተያያዘ ልዩ ልዩ አጃኢብ የሚያሰኙ ነገሮችን እንሰማለን። አንዳንዴም አትሙች ያላት ነፍስ የሚያስብሉ ወቸው ጉድ የሚያሰኙ ሁነቶች ይከሰታሉ።

የተፈጥሮ አደጋ ምንጮች ከሆኑት ደግሞ መብረቅ አንዱ ነው። ከዚሁ ጋር የተያያዘ አንድ ሰሞነኛ መረጃን እንነግራችኋለን። ነገሩ በተቀመጠበት በጨዋታ ላይ ሳለ መብረቅን ስላስተናገደ ሰው ይሆናል።

እንግሊዛዊው የ33 ዓመት ሰው ከመብረቅ ጋር በተያያዘ የተለየ ነገር እንደገጠመው ነው የተሰማው። አይዳን ሮዋን የቪዲዮ ጌም ፕሌይ ስቴሽን በመጫወት ላይ ነበር።

እየተጫወተ የሆነ አንዳች ከባድ ስሜት እንደተሰማው ይናገራል። ይህ ግን በመብረቅ መመታት ነው ብሎ አልጠረጠረም በርግጥ መብረቅ ከውጭ የጮኸ እንደሆነ ተሰምቶታል።

አይዳንን የገጠመው ነገር ከዚህ ቀደም ከተከሰቱ የመብረቅ አደጋ ሁነቶች የተለየ ነበር። እርሱ ላይ ያጋጠመው ውጤትም ለየት ያለ ነውም ተብሏል።

ስለአደጋው የሚናገረው አይዳን መብረቅ መትቶትም እንደመታው ምንም ያወቀው ነገር አልነበረም። ስለክስተቱም ሲናገር ከውጭ ነጎድጓድ ሰማሁ። ከዚያም በቀኝ እጄ ላይ ሙቀት እና ማቃጠል ተሰማኝ ይላል።

በሰውነቱ ላይ የተከሰተው ከስተት ምን እንደሆነ አለማወቁ ደግሞ ነገሩን የተለየ አድርጎታል። አይዳን ስለሆነው ምንም ስላላወቀ እርጥብ ፎጣም አብሮት ያለውን ሰው እንዲሰጠው ጠየቆ ነበር፤ የእጁ ሙቀት አለልክ በማየሉ እርሱን ለማስታገስ።

አብሮት የነበረው ሰው ግን የቃጠሎ ሽታ እየሸተተው ስለመሆኑ እንደነገረው ሜትሮ በዘገባው ያትታል። አብሮት የነበረው ሰውም በመብረቅ ተመትቶ ቆስሎ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠሯል።

እርሱ ላይ ስለሆነው ያላወቀው አይዳን ሮዋን በወዳጆቹ ጉትጎታ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ። ወደ ድንገተኛ ክፍል የገባው ሮዋን በዘጠኝ ዶክተሮች ምርመራ ከተደረገለት በኋላ እውነትም በመብረቅ ተምትቷል ሲሉ አረጋገጡ።

የልብ ምቱ መደበኛነቱ አጥቶ የነበረ ቢሆንም በዚያ ሁነት መረጋጋቱ ክስተቱ ሌላ ግርምትን የሚያጭር እንዲሆን አድርጎታል።

ወደ ሆስፒታል የተወሰደው አይዳን ቶሎ የልብ ምቱ መስተካከል ችሎ በግራ እና ቀኝ እጁ ላይ የተቃጠለው በግልጽ ቢታይም ሌላ ሰውነቱ ግን ደህና ሆኗል። ሁኔታው ግን ብዙዎችን ወቼው ጉድ አሰኝቶ አልፏል።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-19