ሀገሬ ቲቪ

ሴቶች ለመጀመሪያ ግዜ የተሳፉበት ምርጫ

በአለማችን የ ፖለቲካ ሰርአት ወስጥ በአበዛኛው የ ወንዶች ተሳትፎ በልዩነት ይታያል ። ነገር ግን የአለም የፖለቲካ መድረክ ለሴቶች እምብዛም እንዲሳተፉ እድል ሲሰጥ አይስተውዋልም ።

ጊዜው 1886 አም ነው የ 19ኛው ከፍለ ዘመን መገባደጃ በኒውዚላንድ ከወትሮ የተለያ እንቀስቃሴ መታየት የተጅመረበት። ይህም እንቀሰቃሴ እኛ ሴቶች በምርጫ እንሳተፋለን መንግስታችንን እንመርጣለን የሚል እንደምታን የያዘ ነበር ። የሴቶች በፖለቲካ መደርክ የ እንሳተፍ ጥያቄ በ አወሮፓ፣ በአሜሪካ በእንቅሰቃሴ ደረጃ የተጀመረ ቢሆንም እንደኒውዚላንድ የተጠናከረ አልነበርም ።

መላው አለም ሴቶችን በፖለቲካው መድረክ እንዳይሳተፉ አገዶአቸው ቆይቷል ። በተልምዶ አባባል ሴቶች የቤት እመቤት እንዲሁም ልጆችህን የመንከባብከብ ግዴታ ወስጥ ከቷቸው ቆያቷል ።

በኒውዚላንድ የተጀመረው የ ሴቶችህ የመምርጥ እንዲሁም በፖልቲካው የመሳተፍ ጥያቄን ይበልጥ እንዲቀጣጠል አንድ አጋጣሚ ተከሰት ይህም ክስተት በ 1879 አም የተበራከተው የአልኮል መጠጥ እና ኢንዱስትሪው በበዛት መክፈትመጀመር ነው።

ከዛም ሲሻገር መጠጥን አብዘተው መጠጣት ያዘወትሩ የማሀበረሰብ ከፍሎች ሴቶች እና ህጻናትን መበደል ጀመሩ። ይህ ከስተትም ሴቶችን ወደ አደባባይ እንዲወጡ አሰገደደ።

በዚህን ወቅት ነበር ምሰረታወን አሜሪካን ያደርገው የሴቶች ክርስቲያን ቴምፕሪያንስ ህብረት በ1878 አም በኒውዘላንድ ቅርንጫፉን ከፈተ። ይህንንም ህብረት በኒውዘላንድ ማሰተባበሪያ ኬት ሼፓርድ የትባለች እንግሊዛዊት ተመራው ጀመር ።

ኬት ሼፓርድም ሴቶችህ መምረጥ ይችላሉ በሁሉም ፖልቲካዊ እንቀሰቃሴዎች ወስጥም ይስታፉ ሰትል እንቀሰቃሴውን አቀጣጠልችው። ለህገሪቱ ፓርላማም በትደጋጋሚ ግዜ የሴቶች የመምረጥ እና የፖልቲካን ተሳትፎ የሚጠይቅ የአቤቱታ ደብዳቤዎችን ታስገባም ጀመር ።

በ1886 ኬት ሼፓርድ እና ህብረቱ በአወሮፓ እንዲሁም በኒውዚላድ የሚገኙ ጎልማስ ሴቶችን ፊርማ ማሰባብሰብ ጀመሩ ከአጠቃላይ ሴቶችም አንድ አራትኛ የሚሆነውን ፊርማ ማገኝት ቻሉ ።

በዛኑ ወር መሰከርም 8 1886 የሴቶች የመምረጥ እንዲሁም የፖለቲካ ተሳትፎአችውን የሚያረጋገጠው ረቂቅ ህግም ለፓርላማው ቀረበ። በወቅቱ የነበሩት የሃገሪቷ ጠቅላይ ሚንሰተር ሪቻርድ ሴዶን ይህን ህግ ተቃውመት የነበር ቢሆንም በፓርላማው በነበረ የድምጸ አሰጣጥ ሂደት ግን 20 ለ 18 በሆነ ደምፅ ሴቶችን የመምረጥ መበት የሚያጎንጽፈው ህግ ጸደቀ።

ይህንንም ህግ መስከርም 9 1886 የኒውዘላንዱ ገዥ ሎርድ ገላስኮም ሴቶች መመርጥ እንደሚችሉ በፊርማችው አረጋገጡ። በዛው አመት መጨረሻ ሀዳር 20 1886 አም ላይ የኒውዘላንድ አጠቃላይ ምርጫ ከመካሄዱ ሰድስት ሳምንታት ቀድም ብሎ 84% የሚሆኑ የኒወዘላንድ ሴቶች ምዘገባ አጠናቀምው ነበር ።

ለምርጫው ደምጽ ለምሰትጠትም ተመዘግበው ከነበሩት ሴቶችም ሁለት ሶሰተኛው የሚሆኑ ሴቶችም ለመጀምሪያ ግዜ ደምጽ ሰጥተዋል ። በዚህም ምክያት ኒውዝላንድ የመጀመሪያዋ ለሴቶች የመምረጥ መብትን የስጠች ሃገር አሰኝቷታል ይገኛል።

ታዲያ ከዚ በኋላ ነው የትቀሩት የአለም ሃገራት ለሴቶች የመምረጥ መብትን መስጠት የጀመሩት ፣ ለአብነትም ካናዳ 1910አ.ም ፣ በሪታኒያ 1911 እንዲሁም አሜሪካ 1913አ.ም።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-19