የ አ/አ የምግብ ፤ የመድሀኒት ፤ የጤና ክብካቤና ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማዋ ያለውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ የቁጥጥር ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቼ እየሰራው ነው ብሏል።
በዚህም መሰረት ባሳለፍነው 2014 ዐ.ም ከስነ ህንጻ ፤ ከሞያዊ ትግበራ ፤ ከግብአት አቅርቦት እንዲሁም ከባለሞያ አንጻር 2537 ተቋማት ላይ ግምገማ ያኪያሄደ ሲሆን ለህብረተሰቡ ጎጂ ናቸው ባላቸው የተለያዩ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት 33 መለስተኛ ክሊኒኮች ፤ 196 መካከልኛ ክሊኒኮች ፤ 103 መድሀኒት መደብሮች ፤ 178 ልዩ ክሊኒኮች እንዲሁም 5 ሆስፒታሎች በተቋማት ደረጃ እርምጃ እንደተወሰደባቸው በባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አምደየሱስ አድነው ተናግረዋል ።
ማህበረሰቡ በማንኛውም አገልግሎት ቅሬታ ወይም ጥርጣሬ ከተሰማው በአቅራቢያው ወዳለ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ጽ/ቤት በመሄድ ወይም በነጻ የስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-09-19
