ሀገሬ ቲቪ

ኢ-መደበኛ የሰዎች ዝውውርን ለመቀነስ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን እየተሻሻሉ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ኢ-መደበኛ የሰዎች ዝውውርን ለመቀነስ ከፖሊሲ ጀምሮ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን እየተሻሻሉ ነው ተባለ። ይህ የተባለው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 11 ሀገራት የተሳተፉበት የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም ላይ ነው ።

በመድረኩ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል “ወጣቶችን ብቁ በማድረግ ፣ በክህሎት እና ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ መሥራት ካልተቻለ የኢ- መደበኛ የሰዎች ዝውውር ችግሮችን መቀነስ እንደማይቻል ኢትዮጵያ ታምናለች” ብለዋል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-19