ሀገሬ ቲቪ

“ኮቪድ 19 እያበቃለት ነው” ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የኮቪድ 19 ቫይረስ በአሜሪካ ውስጥ እያበቃለት ነው ሲሉ ተናገሩ። በወረርሽኙ በርካታ ዜጎቿን ያጣችው አሜሪካ አሁንም ከ ኮቪድ ጋር የምታደርገው ትግል የቀጠለ ቢሆንም ከምናየው ነገር አንጻር ኮቪድ እያበቃለት ነው ማለት እንችላለን ብለዋል።

በቀጣይ ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች ለመዘጋጀት ምክር ቤቱ 22.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲመድብ ጠይቀዋል ።

ፕሬዝዳንቱ ይህን ቢሉም የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ በሀገሪቱ በየቀኑ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት እንደሚሞቱ አስታውቋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-19