ሀገሬ ቲቪ

የተባበሩት መንግሥታት ለትምሕርቱ ዘርፍ የሚያደርገው ድጋፍ

የተባበሩት መንግሥታት 2023 የሚጀመር እና በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የትምሕርት ሥርዓቱን ለመደገፍ የሚውል ፕሮጀክት አጸደቀ።

በተጠቀሰው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ ለዚህም እንዲረዳ 2 ቢሊዮን ዶላር መነሻ በጀት ተይዟል።በ2030 ደግሞ ይኽው በጀት ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ዥንዋ የተሰኘው የዜና ምንጭ ዘግቧል።

የተማሪዎችን ክህሎት ማሳደግ እና ለትምሕርት ቤቶች ድጋፍ የሚያደርገውን ፕሮጀክት የተመድ ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጎተሬዝ እና የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛቸው ጎርደን ብራውን በይፋ አስጀምረውታል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-19