ዐለም አቀፉ የስነ ምግብ ድርጅት የሆነው ኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል እና የ ኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ በፎሊክ አሲድ እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ በፎሊክ አሲድና በ አዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው ምርት በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ገበያ ለማቅርብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።
በርካታ ሀገራት ምግቦችን በፎሊክ አሲድ የማበልጸግ መጠነ ሰፊ ስራ በመስራታቸው በ እጥረቱ የሚከሰቱ ችግሮች በእጅጉ መቀነሳቸውን ተናግረው በኢትዮጵያ ግን ለ ጉዳዩ በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ ይህ ችግር በብዛት እንደሚከሰት አክለዋል።
ይህ ፕሮጀክት 25 ሚሊዮን 320ሺ በወሊድ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶችን እንዲሁም 11 ሚሊዮን 653 ሺ ታዳጊ ልጃገረዶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-09-20
