ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻውን 129 አደረሰ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አንድ መዳረሻን በመጨመር የመዳረሻዎቹን ቁጥር 129 አደረሰ። ወደ ጆርዳን ዋና ከተማ አማን ነው አዲስ መዳረሻ የጨመረው። አዲሱ መዳረሻው በመካከለኛው ምስራቅ ለአየር መንገዱ 13ተኛው ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት መስፍን ጣሰው በበረራ ማስጀመሪያ ስርዓቱ እንደተናገሩት ዓየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት የመዳረሻ ቁጥሩን እያሳደገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-20