ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ እና ቻይና ምክክር በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ

ኢትዮጵያ እና ቻይና በኢኮኖሚ እና በዓለም አቀፍ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት መከሩ።

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ በኒውዮርክ መክረዋል።

እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ እየተሳተፉ ያሉት አቶ ደመቀ መኮንን እና የቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ በኢኮኖሚ እና በዓለም ዓቀፍ የባለብዙ ወገን መድረክ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ነው የተነጋገሩት።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የልማት ትብብር እንዲሰፋ በተለይም ቻይና በቀጠናው በልማት እና ሰላም የምታደርገውን አስተዋፅዖ እንድታሳድግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጠይቀዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-20