ሀገሬ ቲቪ

በዩጋንዳ አንድ ሰው በኢቦላ ሞተ

ዩጋንዳ አዲስ በኢቦላ የተጠቃ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች። በማእከላዊ ዩጋንዳ የሚኖር የ24 ዓመት ወጣት በቫይረሱ ሳቢያ መሞቱን አረጋግጫለሁ ሲል የሀገሬው የጤና ሚንስቴር አስታውቋል።

ግለሰቡ የኢቦላ ምልክቶች ይታዩበት እንደነበረ የጤና ሚኒስቴር ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ አክሏል። ሌሎች ምልክት የታየባቸው 8 ሰዎችም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ስለመሆኑ ተሰምቷል።

በዩጋንዳ የሱዳን እና የዛየር ዝርያ ያላቸው የኢቦላ አይነቶች ከዚህ ቀደም ተከስተው እንደነበር አይዘነጋም።

በሳምሶን ገድሉ
2022-09-20