ሀገሬ ቲቪ

ባለቤቴ የሰውነት ክፍሌን ሸጦብኛል ያለችው ግለሰብ

ሰርቆት በዚህ ደረጃ ይፈጸማል ቢባል ማን ያምናል ። ዛሬ አንድ ጉድ አየሚያሰኝ የስርቆት ተግባርን እንንገራችሃለን ።

ሁነቱ የተፈጠረው በህንድ ኮዳሚታ በምትባል ከተማ ወስጥ ነው በሕንድ የምትኖር አንዲት ሴት ባሏን በስርቆት ከከሰሰች ይቺ ሴት ባሏን የከሰሰስችው በተለመደ የሰርቆት ወንጀል አይደልም።

የገዛ ባሌ አንዱ ኩላሊቴን ሰርቆ በጥቁር ገብያ ሸጦብኛል ሰትል ከሳዋልች። ራንጂታ ኩንዱ ተባላለች በመካከልኛው የእድሜ ክልል ወስጥ የምትገኝ ሲሆን በህንድ ኮዳሚታ በመትባል የገጠር ከተማውሰጥ ተኖራለች ይቺ ሴት ባለቤቴ ከ 4 አመት በፊት የገዛ ኩላሊቴን ሰርቆ ሸጦበኛል ተላለችህ ።

የኩላሊቷን አንድ በቻ መሆን ያወቀችው በሆድ ህመም ለሀክምና ሆስፒታል ባመራችበት ወቅት ነው ።ሴትየዋ እንደምትለው በ2018 የኩላሊት ጠጠርን ለማሰወገድ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ወደ ሆሲፒታል ባለቤቷ እንደ ወስዳት ነገር ግን ባለቤቷ አንዱን ኩላሊት ለማወጣት እንዳሰበ እና ዝጅት አደርጎ እንድንደ ነበር እና በ በጥቁር ገብያው እንደሽጠባት ተናገራለች ።

“በማደንዘዣ ወስጥ በመሆኔ ኩላሊቴ ሲወስድ ሙሉ በሙሉ አላውቀውም ነበር። ባለቤቴ ኩላሊቴን ከወሰድም በኋላ በአቀራቢያችን በምትገኝው ኤም ቪ- መንደር በጥቁር ገብያ ሸጧል ሰትል ተናገራለች።”

ፕራሳንት ኩንዱ በመባል የሚታወቀው ራንጂታ ባለቤት በመንደሯ ውስጥ ሕገ ወጥ ስደተኛ ሆኖ የቆየ የባንግላዴሽ ዜጋ እንደሆነ እና በትዳር ዓለምም ለ12 ዓመታት የቆዩ ሲሆን ሁለት ልጆችንም አፍርተዋል ። ከስምንት ወራት በፊት ቤተሰቡን ጥሎ ከሌላ ሴት ጋር ትዳር እንደመሰርተም ትናገራለች ።

የካሊንጋ ቴሌቪዥን እንደዘገበው ድርጊቱ በተፈፀመበት ሰዓት አካባቢ ባልና ሚስቱ ከጥሎሽ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ እየተጨቃጨቁ ነበር። ባልየውም የራንጂታ ኩላሊቱን ለመስረቅ ና ለመሸጥ የወሰነው በጥሎሹ ወቅት የነበርበትን እዳ ለመክፈል በማስብ እንደሆነ ጣቢያው አስታወቋል ።

ራንጂታ ኩንዱ የሐሰተኛ ሰነዶች በማዘጋጅት ኩላሊቴን ሸጠዋል በማለት በባሏን እና በአማቷ ላይ ክስ አቅርባለች።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፖሊሶች ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳዩን እየመረመሩ እንዳሉ ተንገሯል። የአከባቢው ፖሊሶችም ተጠርጣሪዎች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እርምጃ ይወሰደባቸዋል ሲሉ ሃስባቸውን ሰጥተዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-20