ሀገሬ ቲቪ

የዓለም አቀፍ ጸረ ሽብር ዘመቻ የተጀመረበት

አሜሪካ ዓለም አቀፍ የጸረ ሽብር ዘምቻን ከዛሬ 22 ዓመት በፊት ብታስጀምርም ኦሳማ ቢላደንን ከመግደል የዘለለ ውጤት አላመጣችም የሚሉ አሉ።

ብጆርጅ ደብሊው ቡሽ አቅራቢነት በአሜሪካ ምክርቤት የተወስነው ይህ ወሳኔ ሀገሪቱ ያለልክ በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንድትገባ አድርጓታልም የሚሉ አሉ።

እነዚህ አካላት ለዚህ በማሳያነት የሚያቀርቡት በኢራቅ ፣ በአፍጋኒስታንና በሶሪያ ጦሯን ማዝመቷን ነው። ጸረ ሽብር ዘምቻው ከመስካት ይልቅ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሽብርተኞች እንዲያንሰራሩ አድርጓልም የሚሉ ተክራካሪዎችም አሉ ።

ቦኮሃራም አልሸባብ አይኤስ አይኤስ የተፈጠሩት ከዚህ ዘመቻ በኋላ ነው በሚል። ሀሳቦች በተለያየ መልኩ ቢነሳም አሚሪካ ግን ዓለም አቀፍ የጸረ ሽብር ዘምቻን ከዛሬ 22 ዓመት በፊት በማስጀመር በመስከረም 11 ለደረሰባትን ጥቃት አጸፋ ምላሽ መስጠቷ ይወሳል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-20