ሶቪየት ከመፍርሷ በፊት በመጨረሻ የነበርው የጎሳ የመክፋፈል ሁኔታ እንዲሁም በባልሰጣናቱ መካከል የነበርው ሽኩቻ ሶቪየት በውስጧ የሚገኙ የቀድሞ ገዛቶቿ እራሳቸውን ችለው ሃገር እንዲሆኑ ምክንያት ሆነ ።
የመጨርሻው የሶቪየት መሪ የነበሩት ሚሃኤል ጎርባቾቭ በ1980ዎቹ የለውጥ እንቀሰቃሴዎችን በማስተዋወቅ አርመናውያን በሶቪየት አገዛዝ ሥር የተሻለ ሕይወት እንደሚመሩ ቃል ገቡላቸው።
በናጎርኖ-ካራባክ የሚኖሩ አርመናውያን፣ በጎርባቾቭ ቃል ቢገባላቸውም አርሜንያዊያን ግንጋር ሃገር የመሆን እንቅስቃሴቸውን አላቆሙም ።ይህ እንቅስቃሴ ለአርመን ብሔራዊ ንቅናቄ (AMN) መፈጠር ምንያት ሆነ አብዛኛዉ የአርሜንያ ህዝብም ስለ ነጻነት እንዲያሰብ ተደረግ ።
የካቲት 20 ቀን 1981 ዓ.ም. የናጎርኖ-ካራባክ አርመኒያዊያን ሶቭየት ከአርመንያ ጋር አንድ ለመሆን ድምፅ ሰጡ። ይህ በእንዲ እያለ በናጎርኖ-ካራባክ እና በአዘርባጅን መካከል በ ሚገኙ ህዘቦች መካከል የጎሳ ግጭት ተፈጠረ ።
ይህም የጎሳ ግጭት ወደ ጦርነት ተሸጋገረ። የአርሜንያ ሠራዊትም ከጊዜ በኋላ ናጎርኖ ካራባህን የሚገኘውን መሬት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ ግዛቱን ከአርሜንያ ጋር አንድ ክልል አደርገ።በዚህ ጦርነትም በሺዎች የሚቆጠሩ አርመናውያን ህይወታቸውን አጥተዋል ።
በ1982 ዓ.ምም የተጣለው እገዳ የአርመን ኢኮኖሚን በበዙ ጎድቷታል ፤ በዚህም ምክንያት የኑሮ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አርመናውያን ወደ ተለያዩ ሃገራት እንዲሰደዱም ምክንያት ሆኗል።
ሶቭዪት በመጀመሪያው የ አለም ጦርንት ወቅም በምአራብ ሶቪየት ክልል አከባቢ ከባድ ወጊያን አካሂዳ የነበር ይህም የቀድሞዋን የሶቪየት አካል የአሁኗን ነጻ ሃገር አርመኒያን ከፉኛ አፈራርሷት ነበር ።
በ1981 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከበርካታ የሶቭየት ግዛቶች የመጡ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ አርመናውያን በዬሬቫን ትያትር አደባባይ በአሁኑ ወቅት የነፃነት አደባባይ ላይ ሰልፎችን አደርጉ።
በ1983 አም ላይ በተካሄደም ምርጫ የአርመንያ ብሄራዊ ነቅናቄ ኤ ኤም በፓርላማ ውስጥ ብዙኃኑን ድምጸ ማሸነፍ ቻለ ። አርሜንያም ነሐሴ 23, 1983 ሉዓላዊነቷን አወጀች፤ ከ አንድ አመት በኋላም መስከረም 23, 1984 ላይ ነፃ ሃገር መሆኗን ለ አለም አስታወቀች። በጥቅምት ወር መጀምሪያም አርምኒያ እንደ ሃገር የመጅመሪያውን ፕሬዝዳንት ሌቨን ቴር ፔትሮስያን ፕሬዚደንት አድርጋ መርጠች።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-21
