ሀገሬ ቲቪ

በኢትዮጵያው ሰላም በሚሰፍንበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ በኒዮርክ ሊካሄድ ነው

አሜሪካ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በሰላማዊ መንገድ በሚፈታበት ሁኔታ ላይ ከአፍሪካ ህብረትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በኒውዮርክ ምክክር ልታደርግ ነው፡፡

አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ በአጋርነት እየሰራች እንደሆነ ገልጻለች፡፡

የኒውዮርኩ ውይይት የሚደረገው የኢትዮጵያ መንግስትና በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ተማምነው በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር እንደሆነ በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛው ማይክ ሃመር አስታውቀዋል፡፡

ማይክ ሃመር ሀገራቸው ዲፕሎማሲያዊ መሳሪያዎችን ሁሉ በመጠቀም ችግሩ በንግግር እንዲፈታ ጥረቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-21