ሀገሬ ቲቪ

በደቡብ ክልል ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የግማሽ ቢሊየን ብር የበጀት ጥያቄ ቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚያካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የግማሽ ቢሊየን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ። ቦርዱ ለኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርበው ይህ የ 541ሚሊየን ብር በጀት በስድስት ዞኖችና በአምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ማስፈጸሚያ ነው።

ቦርዱ ህዝበ ውሳኔውን ለማስፈጸም የድርጊት መርሐግብር ያዘጋጀ ሲሆን ተግባራቱን ለመከውን ያስፈልግኛል ያለውን በጀት ነው እንዲፈቀድለት ነው ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያቀረበው።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-21