የዓለም ጤና ድርጅት የኦሚክሮን እና የዴልታ ቫይረስ በጋራ የኮቪድ -19 ሱናሜ ሊፈጥሩ ይችላሉ አለ፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መስፋፋት በተዳከሙ የጤና ተቋማት እና ስርዓት ላይ የበለጠ ጫና ሊያደርስ ይችላል ሲሉ የአለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የኦሚክሮን እና ዴልታ ኮሮናቫይረስ በጋራ ሱናሜ አሊያም አዲስ መዕበል ሊፈጥሩ ይችላሉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ኮቪድ 19 የዓለማችን ፈተና ሆኖ ባለበት አዲስ እና በመሰራጨት አቅሙ ፈጣን የሆነው የኦሚክሮን ቫይረስ መከሰት ከባድ ችግር ሊፈጥር እንዲሚችል ነው የተጠቆመው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ሪፖርት የተደረገው የኦሚክሮን ቫይረስ አሁን ላይ በአሜሪካ እና በከፊል አውሮፓ የስርጭት አድማሱን አስፍቷል ከ1 መቶ 94ቱ የዓለም ጤና ድርጅት አባል ሀገራት ዘጠና ሁለቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ህዝቦቻቸውን በዚህ አመት መገባደጃ ላይ ለመከተብ ቢያቅዱም ማሳካት ግን አልቻሉም፡፡ በፈረንጆቹ አዲስ አመት ታዲያ ይህን እቅዳቸዉን ወደ 70 በመቶ እነዲያሳድጉ ድርጅቱ አሳስቧል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-30
