ሀገሬ ቲቪ

የማዕድን ሚንስቴር ከፖሊ ጂሲ.ኤል ጋር የነበረን ውል አቋረጠ

የማዕድን ሚንስቴር በነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ከቆየው ፖሊ ጂሲ.ኤል ጋር የነበረን ውል ማቋረጡን አስታወቀ።

ፖሊ ጂሲ.ኤል የተስኘው ኩባያ ከ10 ኣመት በላይ በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ልማት ስራ በኢትዮጵያ ተሰማርቶ ነበር። ይሁን እንጂ የሚፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ውሉ መቋረጡን የማዕድን ሚንስትሩ ታከለ ኡማ ገልጸዋል ።

በቀጣይም የነዳጅ ሀብቱን ወደ ስራ የሚያስገቡ አፋጣኝ ስራዎች ይሰራል ብለዋል ።የዛሬው ውሳኔ ፈቃድ ተስጥቷቸው ወደ ሰራ ለማይገቡ ሌሎች ኩባንያዎችም ማስጠንቅቂያ የስጠ እንደሆነም ሚንስትሩ ተናግረዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-21