በዓለም ላይ ኤድስ ፣ ሳናባና ወባ የሚያደርሱትን ጉዳት እስከ ፈረንጆቹ 2030 ለመቀነስ 18 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ።
ገንዘቡን ለማሰባሰብ እስካሁን በተደረገ ጥረት ከአሜሪካ ከጀርመንና ከጃፓን በጥቅሉ 8 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን ከሚጠበቀው አንጻር ግን በቂ እንዳልሆነ ነው የተገለጻው።
በአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆባይደን መሪነት ከተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉብኤ ጎን በሚካሄደው የገንዘብ ማሰባስቢያ መርሐግብር ግን ተጨማሪ ድጋፍ ከሀገራት ለማግኘት ታቅዷል።
የዓለም አቀፍ ድጋፍ አስተባባሪ ፍራንስዋ ቫኒ በኮቢድ ወረርሽኝ ወቅት የነበረው ሁላችንም ደህና ካልሆንን እኛ ብቻ ደህና ልንሆን አንችልም የሚለው መርህ እነዚህን በሽታዎች ለማጥፋት በሚደረገው ጥረትም ሊተገበር ይገባል ብለዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-21
