የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቲሬዝ በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው ሰብሰባ የበለጸጉ ሃገራት በአየር ንብርት ለውጥ ለሚሰቃዩ ሃገራት ግብር መክፈል አለባቸው ብልዋል ።
የበለጸጉት ሀገራት ከነዳጅ እና ከሃይል ማመንጫ የሚገኘው ሃበት እነሱን እያሳደጋቸው በአንጻሩ አለማችንን ግን ኩፉኛ እየጎዳ ነው ብለዋል።
ጉቲሬዝ በጉባኤው በአየር ንብረት ቀውስ ምክንያት በሚከሰቱ አስከፊ የአየር ሁኔታ ብዙዎች ሞተዋል፣ በተፈጥሮ አደጋዎች ተጎደተዋል።
ሰለዚህ እነሱ በበከሉት ከባቢ አየር ሳቢያ ለተጎዱ ታዳጊ ሀገራት የበለጸጉት ድጋፍ የማስተባበሩን ስራ በንቃት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-21
