ከግማሽ አመት በላይ ያስቆጠረው የሩሲያን የዩክሬን ጦርነት አሁን ወደ ሌላ ምእራፍ የተሸጋገረ ይመሰላል ፤ሰሞኑን የዩክሬን ሃይሎች በሃይል የተያዙ ግዛቶቻቸውን እያስለቀቁ ወደፊት መገስገሳቸውን ሲገልጹ ነበር።አሁን ደግሞ ሩሲያ በመላ ሀገሪቱ ያሉ ተጠባባቂ ጦር ዘምቻውን እንዲቀላቀል ከፊል ቅስቀሳ እንዲካሄድ ወስናለች ።
ፕሬዘዳንት ፑቲን ከዚህ ውሳኔ የደረስ ነው ምእራባውያ የግዛት አንድነቴን ሊያናጉ ህዝቤን ይበልጥ ሊጎዱ ነው በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ ውስሳኔያቸው በሁለት መልኩ እየታየ ነው፤ አንዳንዶች ያሰቡትን አሳክተው የሚፈልጓቸውን የዩክሬን ግዛቶችን በቁጥጥራቸው ስር ስላዋሉ ተጨማሪውን ተጠባባቂ ሃይል በመጠቀም ግዛታቸውን ለማጠናከር ማሰባቸው ተገቢ ነው ነው ሲሉ ሌሎች አቅማቸው መዳከሙንና ሽንፈታቸውን ያሳያል እያሉ ነው ።
በቅርቡ ከፑቲን ጋር ተገናኝተው እንደመከሩ የሚገልጹት የጀርመኑ ቻንሰለር ኦላፍ ሹልዝ ይህ የሽንፈት ጅማሮ ሩሲያ ጦረነቱን እንደማታሽንፍ እየገባት ነው ብለዋል ፤ ምዕራባውያኑ ያሳስባቸው ግን ተጠባብቂ ጦር ከመጠራቱ በላይ ሁለት ነገር ነው ።
በቁጥጥሬ ስር ባሉ አራት የዩክሬን ግዛቶች ህዝበውሳኔ አካሂዳለው ማለቷ እና ሀገሬን ለመከላከል ሁሉንም አማራጭ እጠቀማለሁ የሚለው የፑቲን ንግግር። ሩሲያ በዶኔስክ፣ በሉዋንስክ፣ በዛፓሮዚያና በኬርሶን አካሂዳለው ያለችውን ህዝበ ወሳኔ ሁሉም ምዕራባውያን እውቅና አንስጠውም ብለዋል።
የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማርኮን ይህ በዲሞክራሲ መቀለድ ነው ይላሉ።በሃይል የተየያዙ እነዚህ ግዛቶች የሚያካሂዱት ህዝበ ውሳኔ ከዩክሬን ይልቅ ሩሲያን የሚመርጡበት ነው በሚል። አሜሪካ በበኩሏይህ ወረራን ህጋዊ ለማደረግ የሚደርግ መፍጨርጨር ነው ብላለች።
ጀርመንም ይህ አለማፈር ነው እንዴት በሰው ግዛት ገብቶ ህዝበ ወሳኔ ይካሄዳል ባይናት። የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌላቭሮቭ ግን ጉዳዩ የግዛቶቹ ነዋሪዎች እንጂ የማንም አይደለም ባይ ናቸው።
“እኛ እያልን ያለነው በየግዛቱ ያሉ ሰዎች ይወስኑ ነው እነርሱ ናቸው የነገ እጣ ፋንታቸውን የሚያረጋግጥ ወሳኔ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አያይዘው መወሰን ያለባቸው”
ምዕራባውያኑ ግን ሩሲያ በህዝበ ውሳኔ ስም ከዐመታት በፊት ወደ ግዛቷ እንደጠቀለለቻት ክሬሚያ እነዚህንም ልትጥቀልል ነውና አለም ሊፈቅድላት አይገባም እያሉ ነው ፤ ግን ዩክሬንን ከመደገፍ ውጭ ደፍረው የተጠናከረ እርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ አይጠበቅም።
ለዚህ ደግሞ ፑቲን ሁሉንም አማራጮች ለሃገሬ ህልውና ስል ዕጠቀማለሁ ማለታቸው ዋነኛ ምክንያታቸው ለምን ቢሉ ሩሲያ የኒኩለር ባለቤትናትና ።የከፋ ከማጣ እርሱንም ቢሆን ከመጠቀም ወደኋላ አትልም የሚል ስጋት አላቸው። ፑቲን ግን ይህን አይቀበሉም እንደውም ምዕራባውያኑ ከኒኩለር ጋር በተያያዝ የእኛን ሰም ለማጥፋት እየሰሩ ነው በሚል ይወቅሳሉ።
ኒኩለር ጥቅም ላይ አይውልም ሲሉ ግን የተሰማ ነገር አለመኖሩ አሁንም ነገሩን ከስጋት ነጻ አላደረገውም ።ግን ምክያቱ ምንም ይሁን ምን 3መቶ ሺ የሚደርስ ተጠባባቂ ጦር መጥራታቸው ከዩክሬን ጋር የገቡበት ጦረነት ባሰቡት ልክ ቀላል እንዳልሆነላቸው ነው።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-21
