
77ኛው የተመባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒውዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። ከ2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል በተካሄደው በዚህ በ 77ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዐለማችን ያስተናገደቻቸው ክስተቶች በሰፊው ተነስተውበታል ።
በዚህ ጉባኤ የሴኔጋል ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል አፍሪካ በዐለም መድረክ ላይ የተሻለ ውክልና ማግኘት ይገባታል ሲሉ ለጉባኤው በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
“የአፍሪካ ህብረት በቡድን 20 ውስጥ መቀመጫ እንዲሰጠው ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ጥያቄ በድጋሜ ላስታውስህ እፈልጋለሁ። 1.4 ቢሊየን አፍሪካውያንን የሚመለከቱ ውሳኔዎች በሚተላለፉበት ጊዜ አፍሪካ በቦታው ላይ መገኘት አለባት” ብለዋል ።
ፕሬዝዳንቱ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ፤ የ አየር ንብረት መለዋወጥና በተለያዩ አካባቢዎች እየተነሱ ያሉት ደም አፋሳሽ ግጭቶች የዐለምን ሁኔታ በጣም አስከፊ እያረገው ነው በተለይም ሽብርተኝነት ለብዙዎች ስጋት ደቅኗል ሲሉም ተደምጠዋል ።
“በአህጉሪቱ ላይ ሽብርተኝነት መስፋፋቱ የአፍሪካ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ይህ ጉዳይ ከአፍሪካ አልፎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዋና ዕይታ ስር የሚወድቅ አለም አቀፍ ስጋት ነው ። የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ግጭቶችን በሌሎች ሀገራት እንዳሉ ግጭቶች ለመፍታት የሚወስደዉን ተመሳሳይ መንገድ መጠቀም አለበት።”
ሊላው በሩሲያና ዩክሬን መካከል በሚደረገው ጦርነት አፍሪካውያን ወገንተኛ እንዲሆኑ የሚደረግን ጫና በመጥቀስ አፍሪካ “የአዲሱ ቀዝቃዛ ጦርነት የመራቢያ ቦታ መሆን አትፈልግምም” ሲሉ ተናግረዋል ።
ፕሬዝዳንቱ ዚምባብዌ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መነሳት አለበት የሚል ጥያቄ አቅርበዋል ። ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣሉት ማዕቀብ በዲሞክራሲያዊ እና በሰብአዊ መብት ማሻሻያ ሂደት ላይ ለዉጥ ባለማሳየቱ እንዲሁም የፕሬስ ነፃነቶችን መገደብ በሚሉት እንዳላነሱት ይታወቃል።
በዚምባብዌ ላይ የተጣለዉ ማዕቀብ በኩባንያዎች ፤ በፕሬዝዳንት ኤመርሰን እንዲሁም በበርካታ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነዉ ። ዚምባብዌ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የተነሳ የኢኮኖሚ ቀውስ አጋጥመውታል:: እየተወሰደባት ያለው እርምጃም የህዝቡን ስቃይ እያባባሰ ነው የሚል ትችት ሰንዝረዋል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-09-22